ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk


2.1 by ብራና አፕስ Birana Apps
Oct 31, 2020 پرانے ورژن

کے بارے میں ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና በቅብዐት እምነት መካከል ያለውን ልዩነት የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው ።

«ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ» በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ዶግማ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ከ፲፪ መጻሕፍት በላይ ተካተውበት የቀረበ የመጻሕፍት መድብል ነው።

ይህ የመጻሕፍት መድብል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትርጓሜ ሊቃውንት የተራቀቁባቸውን እና የተጠበቡባቸውን ሲወርዱ ሲወራረዱ ለእኛ የደረሱ የትርጓሜ መጻሕፍት የተካተቱበት ነው። በሦስት ዐበይት ክፍሎች የተመደቡ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ያካተተው ይህ መድብል ምክርና ተግሳጽንም የያዘ ስለሆነ ብዙዎች እንደሚወዱት ተስፋ እናደርጋለን። በአዘጋጁ ታትመው የቀረቡና እና ለኅትመት ዝግጁ የሆኑ መጻሕፍትም የተካተቱበት ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል። በአዘጋጁ ከቀረቡ መጻሕፍት መካከል በቅብዐት ምንፍቅና አማኞች ለተጻፉ መጻሕፍት ተገቢ ምላሽ የተሰጠባቸውን «ደብረ አሚን - የሃይማኖት ተራራ» እና «ፍኖተ ጽድቅ - የእውነት ጎዳና» አካተናል። ከዚህ በተጨማሪም አዘጋጁ የጻፋቸው የተለያዩ ወጎች፣ ትምህርቶችና ግጥሞችም ምክርና ተግሳጽን በስፋት አካተው ቀርበውበታል። ከእግዚአብሔር ለምን እንርቃለን? እግዚአብሔርስ ከእኛ ለምን ይርቃል? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመልስ እና ወደ ንስሐ የሚመራ «ለምን ርቀህ ቆምህ?» የተሰኘው የአዘጋጁ መጽሐፍም በዚሁ መድብል ውስጥ የተካተተ ነው። እነዚህ የአዘጋጁ መጻሕፍት ገበያ ላይ የማይገኙ መሆናቸው ይህን መተግበሪያ ልዩ ያደርገዋል።

ይህ መተግበሪያ በተጨማሪነት ቤተ ክርስቲያናችን ከዓመት እስከ ዓመት የምትገለገልባቸውን ድንቅ መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውንና መጽሐፈ ስንክሳርን ያካተተ ነው።

ይህ መተግበሪያ የያዛቸው መጻሕፍት ዝርዝር

፩. የአንድምታ ትርጓሜ ክፍል

- የጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ።

-የውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።

- የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።

- የአራቱ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ።

፪. የአዘጋጁ መጻሕፍት ክፍል

- ደብረ አሚን

- ፍኖተ ጽድቅ

- ለምን ርቀህ ቆምህ?

- አማኞችን ማጽናትና ማበርታት

- ወጎች

- ትምህርቶች

- ግጥሞች

፫. ሌሎች መጻሕፍት ክፍል።

- ሃይማኖተ አበው

- መጽሐፈ ስንክሳር

- ፍኖተ እግዚአብሔር

میں نیا کیا ہے 2.1 تازہ ترین ورژن

Last updated on Nov 8, 2020
Target API 29 (Android 10) updated

معلومات ایپ اضافی

تازہ ترین ورژن

2.1

اپ لوڈ کردہ

Duc Nguyen

Android درکار ہے

Android 4.0+

رپورٹ کریں

فلیگ غیر موزوں ہے

مزید دکھائیں

ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk متبادل

ብራና አፕስ Birana Apps سے مزید حاصل کریں

دریافت